Telegram Group Search
#Advertisment

እማዬ ሾርባ እና ስቲም ቡና

በልዩ አቀራረብ እና መስተንግዶ በአዲስ መልክ ተመልሰናል።

ሾርባ
ድንች ቅቅል
ቺፕስ(በካቻፕ)
እርጥብ/በአቮካዶ/ካቻፕ/በእንቁላል)
ቡና እና ሻይ
የለውዝ ሻይ
ቀሽር
እንዲሁም እንደምርጫዎ ቢያዙን እናስተናግዶታለን።

አድራሻ አልሚ ምግብ ቤት አጠገብ
0934892799
0980000091
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
-----------------------------
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በDocter of Medicine/MD/ መምህር በቅጥር አወዳድሮ ለመመደብ በቁጥር 0635/02-01/6 በቀን 08/08/2016 ዓ.ም ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልታችሁ ለተመዘገባችሁ ብቻ በቀን 22/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና የተጠራችሁ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

ማሳሰቢያ
-------------
* ለፈተና የሚመጣ ተወዳዳሪ ራሱን የሚገልጽ መታወቂያ ካልያዘ ፈተና ላይ አይቀርብም፡፡
* ማንኛውም ተወዳዳሪ የሞባይል ስልክ ይዞ መግባት አይችልም፡፡
* በሰዓቱ ያልተገኘ ተወዳዳሪ ወደ ፈተና መግባት አይችልም፡፡


ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ
አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስ

@DBU11
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ለ5 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት እና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚንስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት

የ ወላይታሶዶ፣ጋምቤላ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ከሃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣
አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ፤
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፌድራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መስሪያ ቤቶች ውስጥ እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት ውስጥ ተካተዋል።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
#ሆሄ_ተስፋ

አዲስ አበባ - መገናኛ በጣዕም የባህል ምግብ አዳራሽ ተዘጋጅቶ የነበረው የሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት በሙዚቃ እና በስነፅሁፍ ጥበባዊ ዝግጅት ታጅቦ በድምቀት ተጠናቋል።

በዝግጅቱ ላይ የተለዩ እንግዶች የተገኙ ሲሆን
👉የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ተጠሪዎች
👉የመቅረዝ ስነኪን ተጠሪዎች
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ የምንወደዳቸው እና የምናደንቃቸው ገጣሚያን

ገጣሚ ጥላሁን ስማው (የማስተዋል እያዩ "ከፋኝ" ሙዚቃ ግጥም ደራሲ)

ገጣሚት መንበረማርያም ኃይሉ(የቃል ሰሌዳ እና የጊዜ ሰሌዳ የግጥም መድብሎች አዘጋጅ)

የወደ ግጥም ኪነት ተጠሪዎች

እንዲሁም ሌሎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል።

የባህላዊ ምግብ አዳራሽ ባለቤት የሆኑት አቶ ዮሃንስም እንደገለፁት ይህን ዝግጅት በቋሚነት በድርጅታችን በኩል እንዲካሄድ ስንፈቅድ ከልዩ ደስታ ጋር ሲሆን በወር አንድ ጊዜ ለሚደረገው ቋሚ የሆሄ ተስፋ መድረክ ሁሌም በራችን ክፍት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

መገኛውን ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ክበብ በአዲስ አበባ መመስረቱ የተመረቁትን፣በዩኒቨርሲቲ ካሉት ጋር እንዲያገናኝ እንዲሁም አቅምና ክህሎትን በማጎልበት ትልቁን ህልም የሚያሳካ መንገድ እንደሆነ ተገልፁአል።

@DBU11
@DBU_entertain
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ Doctor of Medicine መምህራን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለፈው ወር ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልታችሁ የተመዘገባችሁ ብቻ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና መጠራችሁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተፈታኞች ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ መያዝ እና በሰዓቱ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ማንኛውም ተፈታኝ የሞባይል ስልክ ይዞ ወደ ፈተና መግባት አይችልም፡፡

@dbu11
ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

የምርቃት ጊዜ እንደመቃረቡ እና ጊዜውም አጭር እንደመሆኑ መጠን ለባይንደር እና ህትመት ስራዎች ብዛቱ መታወቅ ስላለበት እንዲሁም የማሰሪያ ገንዘቡ ገቢ መሆን ስላለበት የባይንደር እና የህትመት ፎርም ከዛሬ ሃሙስ ግንቦት 22/2016 ጀምሮ በክፍል ተወካዮች በኩል ለእያንዳንዱ ክፍል ስለሚሰራጭ እስከ ቅዳሜ ድረስ ክፍያውን እንድታጠናቅቁ ስንል እናሳስባለን።

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎች(GC) ኮሚቴ
@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለሴት ተማሪዎች

"ከዚህ ቀደም ባዘጋጀነው የውይይት መድረክ ብዙ ሴት ተማሪዎች ደስተኛ እንደነበሩና በድጋሜ እንዲዘጋጅ በቀረበ ጥያቄ መሠረት አርብ በ23-09-2016 ሴቶቻችንን ያቀራርባል ያልነውን ውይይት አዘገጅተናል"
ዝግጅቱንም ብሎክ 07 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ መታችሁ ተሳተፉ ሲል የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሮክትሬት ጥሪ አቅርቧል።

@dbu11
@dbu_entertainment
2024/05/31 07:27:15
Back to Top
HTML Embed Code: